እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በደህና መጡ!

ይህ ዲጂታል መድረክ መሬትን የሚተዳደርበትን መንገድ በመቀየር ፍትሃዊነትን፣ ግልፅነትን እና ዘላቂ ልማትን ለደመቀች ከተማችን ያረጋግጣል። የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ሥርዓት ሂደቶችን ለማቀላጠፍ፣ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ለዜጎች ለማቅረብ የተነደፈ ነው።

"እንኳን ወደ አዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት በደህና መጡ!"

በከተማችን ውስጥ ቀልጣፋ እና ግልጽነት ያለው የመሬት አስተዳደር ለማድረግ የተዘጋጀውን ይህን የላቀ ዲጂታል መድረክ ስናስተዋውቅ በደስታ ነው። ራዕያችን የመሬት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውልበት፣ የዜጎቻችን ፍላጎት ፍትሃዊና ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ የሚፈታበት የበለፀገ የከተማ አካባቢ መፍጠር ነው። ይህ ሁሉን አቀፍ ሥርዓት የመሬት አገልግሎትን፣ የንብረት ባለቤትነትን፣ የካርታ ኮፒን፣ የስም ዝውውርንእና ሌሎች ከመሬት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመከታተል ያስችላል። የነዋሪዎቻችንን ህይወት ለማሻሻል፣የኢኮኖሚ እድገትን ለማነቃቃት እና ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት እንደሚያስችለንም እናምናለን።
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

በተደጋጋሚ የተጠየቁ አገልግሎቶች

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ለከተማዋ ዜጎች ሰፊ አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት አለበት። በከተማ አስተዳደሩ በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የዋሉ አገልግሎቶች እነዚህ ናቸው።

የስም ዝውውር

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- ካርታ ኦርጅናልና ኮፒ
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- ያገኙበት አግባብ (የፍርድ ቤት፣ የግዢ፣ የውርስ) ወረቀት
- የአገልግሎት ክፍያ
- አምስት (5) ፎቶ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት

🕐 አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 1 ሰዓት

የካርታ ኮፒ

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- ካርታ ኦርጅናልና ኮፒ(ያልጠፋ ከሆነ)
- የጠፋ ከሆነ ማስረጃው ስለመጥፋቱ በህጋዊ አካላት የተሰጠ ማስረጃ
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- የአገልግሎት ክፍያ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት
- አምስት (5) ፎቶ

🕐 አጠቃላይ አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 4 ሰዓት>

የይዞታ መክፈል

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- የሚቀላቀሉትን ካርታዎች ኦርጅናል እና ኮፒ
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- የአገልግሎት ክፍያ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት
- አምስት (5) ፎቶ

🕐 አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 4 ሰዓት

የጀርባ ማህተም

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- ካርታ ኦርጅናል እና ኮፒ
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- የአገልግሎት ክፍያ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት
- አምስት (5) ፎቶ

🕐 አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 4.67 ሰዓት

የይዞታ አገልግሎት ለውጥ

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- ካርታ ኦሪጅናል እና ኮፒ
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- የአገልግሎት ክፍያ
- አምስት (5) ፎቶ
- አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት

🕐 አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 4 ሰዓት​

የባንክ እገዳ መመዝገብ

ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

- በህግ ስልጣን ከተሰጠው አካል የብድር ውል የተደረበት ሰነድ ማቅረብ
- ካርታ ኮፒ(ካለ)
- መታወቂያ ኮፒ(ጊዜው ያላለፈበት)
- ውክልና ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
- የአገልግሎት ክፍያ


🕐 አገልግሎቱ የሚወስደው ጊዜ 1 ሰዓት

አዳዲስ ዜናዎች

የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን የታገደ መሆኑን አሳውቋል። እገዳው ፤ ከሐምሌ 28/2ዐ15 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 5/2ዐ15 ዓ/ም ድረስ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ...

Read More

የመሬት አገልግሎት ዕግድ ተነሳ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ ከቢሮ ሪፎርም ስራ ጋር በተገናኘ በቀን 28/11/2015 ዓ/ም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ የመሬት አገልግሎት መታገዱ ይታወሳል።...

Read More

የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ስም ዝርዝርይፋ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት  ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን...

Read More

የከተማ አስተዳደሩና ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነቡ ነው

የከተማ አስተዳደሩና ሪል ስቴት አልሚዎች ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ወጪ መኖሪያ ቤቶችን ሊገነቡ ነው። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥትና በግል አጋርነት ፕሮጀክት አማካይነት በመረጣቸው ሪል ስቴት አልሚዎች፣ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር...

Read More

የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ስርዓትን በመጠቀም ንብረትዎን ማስተዳደር ይፈልጋሉ?

አሁን ይመዝገቡ እና የመሬት መረጃዎን ያስተዳድሩ። የመሬት አስተዳደር መረጃዎን በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ ይድረሱበት። የህን የመሬት አስተዳደር መተግበርያ በመጠቀም ሁሉንም አገልግሎትዎን በእጅ ስልክዎ ማስተዳደር ይችላሉ።