የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን የታገደ መሆኑን አሳውቋል።

እገዳው ፤ ከሐምሌ 28/2ዐ15 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 5/2ዐ15 ዓ/ም ድረስ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ከቢሮ ሪፎርም ሥራ ጋር በተገናኝ የሚስተካከሉ ስራዎች ስላሉ ነው ተብሏል።

በተጠቀሰው ጊዜ ማንኛውም የመሬት አገልግሎት እንዳይሰጥ በዶ/ር ቀነዓ ያደታ (የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ) ተፈርሞ ለሁሉም ክ/ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የተላከው የእግድ ደብዳቤ ያሳያል።

(ደብዳቤው ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት መረጃ አገልግሎት የተገኘ ነው)

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *